​በኘሪሜየር ሊጉ ድል የራቀው ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ሲዳማ ቡናን ይገጥማል!!!

5ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ እና
 ነገ ቀጥሎ ይውላል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም እስካሁን ምንምጨዋታ ማሸነፍ ያልቻለው ኢትዮጵያ ቡናሲዳማ ቡናን 11 ስአት ከ30 ላይያስተናግዳል።

ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ 9 ሰዓት ላይ ኢትዮኤሌክትሪክ በአዲስ አበባ ስታዲየምአርባምንጭ ከተማን ይገጥማል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሊጉ ከተደረጉ አራትጨዋታዎች መካከል ሶስት ጨዋታ አቻ አንድጨዋታ በሽንፈት አጠናቋል። የዛሬው ተጋጣሚ አርባምንጭ በሜዳውጅማ አባቡናን አሸንፎ የመጀመርያ ሙሉ ሶስት ነጥብ ባሳለፍነው እሁድ ማግኘቱ ይታወሳል። ሊጉ እሁድ ቀጥሎ ስድስት ጨዋታዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን መልካ ቆሌ ላይ ወልድያ በሊጉ መልካም ጅማሮ እያሳየ ያለውን ፋሲል ከተማ ያስተናግዳል። ፋሲል ተከታታይ የሊጉ ሀያል ክለቦች ኢትዮጵያ ቡናንና ቅዱስ ጊዮርጊስን ማሸነፋቸው ይታወሳል።

የፋሲሉ አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ለህክምና ባንኮክ ያመራ ሲሆን ምክትል አሰልጣኙ ቡድኑን የሚመራ ይሆናል። በሌላ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ሶዶ ላይ ከድሬዳዋ ከተማን፣ ጅማ አባቡና ከደደቢት፣ ሀዋሳ ከተማ ከመከላከያ፣ አዲስ አበባከተማ ከ ኢትዮ ንግድ ባንክ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ እሁድ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።

የቅዱስ ጊዮርጊስና አዳማ ከተማ ጨዋታ እሁድ 11 ከ30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል። ሌሎች ጨዋታዎች ሁሉም እኩል 9 ሰዓት የሚጀምሩ ይሆናል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook