​በሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ሙሉ ወጪ የተገነባው 25,155 ተመልካች አቅም ያለው ስታዲየም ጥር 6 በይፋ ይመረቃል፡፡

በስታዲየሙ የምረቃ ዝግጅትን ለማስተዋወቅ በዛሬው እለት በሸራተን  ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የሚድሮክ ግሩኘ ስራአስኪያጅ ዶ/ር አረጋ ሲሆኑየስፖርት ማዕከሉ ጠቅላላ  የቆዳ ስፋቱ 177,000 ሜትር ካሬ ላይ ያረፈ ሲሆን ስታዲየሙ በጠቅላላው 25,155 ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው ነው፡፡

ስታዲየሙ ሙሉ የፀሃይ መጠለያ (Canopy) እና ዘመናዊ ልዩ መብራቶች የተገጠሙለት ነው፡፡ በሀገራችን በዘመናዊነቱ  ተወዳዳሪነቱ የሌለው የአለም አቀፍ የእግር ኳስ  ፌዴሬሽን ማኀበር (FIFA) ደረጀን የጠበቀ ነው፡፡ዙሪያው የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማኀበር የሚጠይቀውን መመዘኛዎች የሚያሟላ ሲሆን በአንድ ጊዜ8 ተወዳዳሪዎችን ማስተናገድ የሚችል መሮጫ ትራክ ያለው ነው፡፡

ከስታዲየሙ በተጓዳኝ የተሟላ ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ማለትም የእጅ ኳስ፤ የቅርጫት ኳስ ፤ የቴኒስ ሌሎችንም ከእንግዳ ማረፊያ ጋር አጣምሮ የያዘ ነው፡፡

የክቡር ትሪቡኑ ህንፃ ባለ ሶስት ፎቅ ሆኖ በውስጡ 4ቡድኖችን በአንድ ግዜ ሊያስተናግድ የሚችሉ ክፍሎች አሉት ፡፡በተጨማሪም ህንፆው የክብር እንግዶች ማረፊያና  ማስተናገጃ ጨዋታዎችን በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን ለማስተላለፍ የሚስችሉ 8 ቻናሎች እና የድምፅ  መከላከያ  (Sound proof )የሆኑ  የጋዜጠኞች ክፍሎች አሉት ፤እንዲሁም ለተመልካቾች ሊቀርቡ እሚችሉ የምግብ ማዘጋጃ  ክፍሎችም ያሉት ነው፡፡ስታዲየሙና የስፖርት ማዕከሉ 308 የአውቶሞቢል ፤14የአውቶቡስ  ፤16  የብስክሌት  ማቆሚያ  ቦታ ከተሟላ የትራፊክ ምልክቶች ያሉት ነው፡፡

የስታዲየሙንና ስፖርት ማዕከሉ ግንባታዎች በአብዛኛው በሀገር ውስጥ ምርቶችና በሀገር በቀል ባለሙያዎች የተፈፀመ ነው፡፡ግንባታው የወሰደው ጊዜ 4 ዓመት ተኩል ነው፡፡ ባላሀብቱ ሼህ ሙሀመድ ለግንባታው ያወጡት የገንዘብ ወጪ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ  (567,890,000) ነው፡፡

ስታዲየሙን ጥር6 ለመመረቅ ቀጠሮ ተይዟለታል::

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook