የጨዋታ ዘገባ | ሲዳማ ቡና በአዳማ ተፈትኖ አሸንፏል።

 

የ13ኛ ሳምንት መርሀግብር አካል የሆነው የሲዳማ ቡና እና አዳማ ከተማ ጨዋታ ቶሎ ቶሎ ግቦች ተስተናግደውበት ባለሜዳዎቹ ተፈትነው 3-2 አሸንፈዋል።

ከባለፈው ሳምንት አሰላለፋቸው ባለሜዳዎቹ የአራት ተጫዋቾች ለውጥ ሲያደርጉ ክፍሌ ኪያ፣ብርሀኑ አሻሞ፣ትርታየ ደመቀ እና አማኑኤል እንዳለ በቋሚ አሰላለፍ ይዘው ሲገቡ። በአዳማ በኩል የሶስት ተጫዋቾችን ለውጥ አድርገው አዲስ ህንፃ፣በረከት ደስታን እና ሚካኤል ጆርጅን በቋሚ አሰላለፋቸው የተጠቀሙባቸው ናቸው።

በርካታ ግቦችን ያስተናገደው የመጀመሪያ አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ረብ የለሽ ቅብብሎችን እንጂ ጥሩ የኳስ እንቅስቃሴ ያልታዘብንበት ነበር። ቢሆንም ግን አዳማዎች የሚያገኟቸውን ኳሶች በቀጥታ ወደፊት አጥቂዎቻቸው በማሻገር እና ኳሶች በሚያገኙበት አጋጣሚ በቀጥታ ወደ ግብ በመምታት በተጨማሪም ከቆሙ ኳሶች ግቦችን ለመፍጠር ሲሞክሩ ተስተውሏል። ለዚህም እንግዳዎቹ ከርቀት በርከት ያሉ የሰነዘሯቸው ውጤታማ ያልነበሩ ጥቃቶች ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ ነበሩ። ሲዳማ ቡናዎች ኳስን በመቆጣጠር የተጋጣሚን ስህተት ተጠቅሞ ግብ የማስቆጠር አማራጫው አድርገው ይዘው ገብተዋል። የደረጄ አለሙ ሲሳይ ሲሆኑ የነበሩት አጥቂዎቹን አነጣጥረው ከመሀል ሜዳ የሚሻገሩ ያልተመጠኑ ኳሶች እንደ አብነት መግለፅ ይቻላል። 4ኛው ደቂቃ ላይ ከመሀል ሜዳ የተላከችለትን ኳስ ቡልቻ ሹራ የሲዳማ ቡና ተከላካዮች ለማጥቃት ወደ ፊት ተጭነው በሚጫወቱበት ወቅት በብቸኝነት ስፍራው ላይ የነበረው ግርማ በቀለን አልፎ ከግብ ጠባቂው ፍቅሩ ወዴሳ ጋር ተገናኝቶ አገባው ሲባል ለጥቂት በአግዳሚው ወጥታበታለች።

ግልፅ የሆነ የተከላካይ ስህተቶች የተስተዋለባቸው ሁለቱም ቡድኖች። በተከታታይ ግቦችን ለማስተናገድ ተገደዋል። አበባየሁ ዮሀንስ ከግራ መስመር ያሻማትን የቅጣት ምት የአዳማ ተከላካዮችን መዘናጋት ተጠቅሞ አማኑኤል እንዳለ በግንባሩ ገጭቶ ግብ በማድረግ ባለሜዳዎቹን መሪ አድርጓል።

ግቧ ከተቆጠረች በኋላ ተጀምራ በፍጥነት ወደ ሲዳማ ቡና የግብ ክልል የደረስችው ኳስ ከቀኝ መስመር ወደ ሳጥኑ የተላከችለትን ኳስ ቡልቻ ሹራ የተከላካዮችን ስህተት ተጠቅሞ ግብ በማድረግ አዳማን አቻ ማድረግ ችሏል።

ከአምስት ደቂቃ በኋላ ሀብታሙ ገዛኸኝ በቀጥታ ወደ ግብ ሲመታ በአዳማ ተከላካዮች ተደርባ ስትመለስ ያገኛት ዳዊት ተፋራ በፍጥነት መልስ በመስጠት መሬት ለመሬት አክርሮ መትቶ ግብ በማድረግ በድጋሚ ባለሜዳዎቹን መሪ ማድረግ ሲችል። ፉአድ ፈረጃ ያሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ በግንባሩ ገጭቶ በቋሚው ለጥቂት የወጣችበት ተጋባዦቹን በድጋሚ አቻ ማድረግ የምትችል አጋጣሚ ነበረች።


ጥንቃቅ ያልታከለበት ጥሩ የኳስ ፍሰትን በማድረግ ወደ ግብ ለመድረስ ጥረት ያደረጉት ሁለቱም ቡድኖች በድጋሚ ግቦችን አከታትለው ለማስቆጠር አልተቸገሩም። 45ኛው ደቂቃ ላይ ዳዊት ተፈራ በሁለት ተከላካዮች መሀል መሬት ለመሬት ሰንጥቆ የላከለትን ኳስ ሀብታሙ ገዛኸኝ በሚገባ ተቆጣጥሮ ግብ በማድረግ ሲዳማ ቡናዎችን ሶስት ለአንድ እንዲመሩ ማደርግ ሲችል። ከአንድ ደቂቃ በኋላ ከቆሙ ኳሶች የሚሰነዘሩባቸውን ጥቃት ለመመመከት ደካማ የነበሩት ባለሜዳዎቹ ግብ ለማስተናገድ ተገደዋል። ከማእዘን የተሻማውን ኳስ ቴዎድሮስ በቀለ በእግሩ መትቶ ግብ በማድረግ በሲዳማ ቡና 3-2 መሪነት ለእረፍት ወጥተዋል።

አዳማዎች እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ የሚያገኟቸውን ኳሶች ከርቀት እየመቱ የተጋጣሚያቸውን ግብ ሲፈትሹ። በረከት ደስታ በግሉ ቡዙ ሜዳዎችን በማካለል በዚህ ጨዋታ ያደረጋቸው ድንቅ እንቅስቃሴ አስደናቂ ነበር። ሲዳማ ቡናዎች አስፈሪ የማይባል ኳሶችን ይዘው ለመጫወት ጥረት አድርገዋል። አዳማዎች 51ኛው ደቂቃ ፉአድ ፈረጃ ሳጥን ውስጥ ይዞ የገባውን ኳስ ወደ ግብ ሲመታ የግርማ በቀለ እግር ጨርፋ ወደ ውጭ በአግዳሚው ለጥቂት የወጣችው አስደንጋጭ ሙከራ ስትሆን። 67ኛው ደቂቃ ዳዊት ተፈራ ኳስ ከሚጀመርበት መሀል ሜዳ በቀጥታ ለአዲስ ግደይ አስረዝሞ ያቀበለውን ኳስ ግብ ጠባቂው ደረጄ አለሙ ቀድሜ ኳሷ ላይ እደርሳለው በማለት ከግቡ ቢወጣም አምበሉ ምኞት ደበበ ከልሎት የነጠረችውን ኳስ ሳይናበቡ ቀርተው ማክሸፍ ሲሳናቸው አጠገባቸው የነበረው አዲስ ግደይ ኳሷን ይዞ በመሄድ ሲያስቆጥር። የአዳማ ቡድን አባላት በእጁ አውርዶ ይዞ ሄዶ ነው ግብ ያስቆጠረው በማለታቸው የእለቱ ዋና ዳኛ አክሊሉ ድጋፊ ግቧን ለማፅደቅ በተነሳው ጭቅጭቅ ግራ በመጋባታቸው ጨዋታው ለአስር ደቂቃዎች ያክል እንዲቋረጥ ምክንያት ሆኖ። በመጨረሻም በአራተኛ ዳኝነት ሲመሩ የነበሩት እያሱ ፈንቴ ረዳትነት በእጁ ነው ኳሷን ይዞ የሄደው በማለት ግቧ ልትሻር ችላለች።

የጨዋታው ዳኞች የሰሩትን ስህተትና የውሳኔ ቁርጠኝነት መጓደል ተከትሎ ከሲዳማ ቡና ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች ተቃውሞ ደርሷቸዋል። ከተቋረጠበት የጀመረው ይሀ ጨዋታ ቡልቻ ሹራ ከሳጥን ውጭ አክርሮ የመታውን ኳስ ፍቅሩ ወዴሳ እንደምንም ተወርውሮ ለጥቂት ያወጣበት ኳስ አዳማዎችን አቻ ልታደርጋቸው የምትችል አጋጣሚ የነበረች ሲሆን።

ከእስማኤል ሳንጋሪ እግር ስር የተነጠቀችው ኳስ ያገኘው ዳዊት ተፈራ ለአዲስ ግደይ አቀብሎት እሱም በድጋሚ ለሀብታሙ ገዛኸኝ አቀብሎት ወደ ሳጥን እየገፋ ገብቶ ከግብ ተጣቂው ደረጄ አለሙ ጋር ተገናኝቶ ያዳነበት ደጋፊውን ቁጭ ብድግ ያደረገችው ደግሞ በሲዳማ ቡናዎች ያለቀላት አጋጣሚ ነበረች። በመጀመሪያው አጋማሽ ከተቆጠረ ግብ ውጪ ተጨማሪ ግቦች ሳይሰተናገዱበት በሲዳማ ቡና 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor