ኢትዮጵያዊው አትሌት የቶኪዮ ማራቶን ባለድል ሆኗል !

14ኛው የቶኪዮ ማራቶን ከደቂቃዎች በፊት ሲጠናቀቅ ኢትዮያዊው አትሌት ብርሀኑ ለገሰ ውድድሩን በበላይነት አጠናቋል ::

 

ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው የቶኪዮ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ብርሀኑ ለገሰ 2:04:15 ሰአት በመግባት የመጀመሪያው ደረጃ ሲይዝ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሲሳይ ለማ በሶስተኝነት ማጠናቀቅ ችለዋል ::

ብርሀኑ ለገሰ ከድሉ በሃላ ሲናገር ” በመጀመሪያ ከ 2:03:30 በተሻለ ማድረግ እችላለሁ ብዬ አስቤ ነበር ወደ ውድድር የገባሁት ሆኖም ግን የግራ እግሬ ላይ በውድድሩ መሀል ህመም ይሰማኝ ጀመረ እናም ህመሙ እየተባባሰ ሲሄድብኝ ድል ማድረግን ብቻ ማሰብ ጀምረኩ ውድድሩን በአሸናፊነት በማጠናቀቄ ደስተኛ ነኝ” :: ሲል ከውድድሩ በሃላ ለጋዜጠኞች አስተያየቱ ሰጥቷል ፡፡

የውድድሩ አሸናፊ 11,000,000 የጃፓን ብር በሽልማትን እንደሚበረከት የቶኪዮ ማራቶን አዘጋጆች ገልፀዋል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor