አቶ እንዳለየሱስ አባተ ከዋሊያዎቹ ሃላፊነት ተነሱ

ከደቂቃዎች በፊት ከታማኝ ምንጭ ባገኘሁት መረጃ የብሄራዊ ቡድኑ ማናጀር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ እንዳለየሱስ አባተ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡ አቶ እንዳለየሱስ የዋሊያዎቹ አለቃ ውበቱ አባተ ወንድም ሲሆኑ የስንብቱ ምክንያት ምን እንደሆነ አልታወቀም፡፡

በውሳኔው ዙሪያ የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሃፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለማመንም ሆነ ለማስተባበል ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ አቶ እንዳለየሱስ በበኩላቸው ውሳኔውን በቀላሉ እንደማያዩት ገልጸው በጉዳዩ ዙሪያ አሁን ምንም መናገር እንደማይፈልጉ ተናግረዋል፡፡

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport