ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገ እትሟ የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት ከተፍ ትላለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ ምን መረጃዎችን ይዛሎት ትመጣ ይሆን?
THE BIG INTERVIEW በሚለው አምድ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በመለያየት መቐለ 70 እንደርታን የተቀላቀለው ዳንኤል ደምሴ የሚላችሁ ይኖራል፤ ዳንኤል ለሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ከሰጠው ምላሽ ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል፡፡
“ቡናን ጠልቼ አላውቅም፤ ክብሬ ተነክቶ ነው የተሰናበትኩት” ሲል ከዛ ውጪም የስታድየምን ሰላም የሚያረጋጉት የፖለቲካ ሰዎች ሳይሆኑ ተጨዋቹ ደጋፊውና የደጋፊው ማህበር ይመስሉኛል፤ ይላል፡፡ ሀትሪክ በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባዋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተደጋጋሚ ሽንፈትን በማስተናገድ ከቻንና ከሌሎች የማጣሪያ ጨዋታዎች ውጪ ስለመሆኑ መረጃን ትሰጦታለች፤ ከዛ ውጪ ደግሞ ለቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋቾች ለምናቀርብላቸው ጥያቄዎች ለነገው እትም መስፍን አህመድ /ጢቃሶ/ ምላሽ ሰጥቷል፤ የፋሲል ከነማው አምሳሉ ጥላሁንም /ሳኛ/ ስለ ቡድናቸው የፕሪ-ሲዝን ዝግጅታቸው የሚላችሁ ይኖራል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዋስ ምንን ታስነብቦት ይሆን በኦልድ ትራፎርድ ማንቸስተር ዩናይትድና ሊቨርፑል ስላደረጉትና አቻ ስለተለያዩበት ጨዋታ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕና ኦሌጉናር ሶልሻየር የሰጡትን አስተያየት እንደዚሁም ደግሞ ለሊቨርፑል የአቻነቷን ጎል ያስቆጠረው አዳም ላላና ከግጥሚያው በኋላ ምን አለ የሚለውን የምናስነብባችሁ ሲሆን ስለ ሊዮኔል ሜሲም የሚወዱት ቃለ-ምልልስ ሊቀርብሎት ችሏል፤ ሀትሪክ ሌሎችንም መረጃዎች ይዛ ነገ ያገኟተታል፤ ሀትሪክ አታምልጦት፡፡
የሀትሪክ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
አስተያየት ይስጡ